ስለ ድርጅታችን
ሪያሊቲ ኮንስትራክሽን እና ሪል ስቴት የተቋቋመው በ2006 (እ.ኤ.አ) ሲሆን አሁን ያለውን ስሙን ያስመዘገበው ግን በ2016 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ) ነው።
የኮንስትራክሽን ስራ እ.ኤ.አ በ2008 በሰበታ ከተማ ጀመርን፤ ከተወሰኑ አመታት በኋላ የመጀመሪያ ፕሮጀክታችንን እ.ኤ.አ በ2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ገነባን።
ከዛ በመቀጠል ድርጅታችን እየተስፋፋ ሌሎች ተጨማሪ ፕሮጀክቶችን፤ እንደ መኖሪያ ቤቶች፣ አፓርትመንቶች እና የንግድ/ቢሮ ህንፃዎችን በአዲስ አበባ መገንባት ጀመረ።
በአሁኑ ጊዜ ሪያሊቲ ኮንስትራክሽን እና ሪል ስቴት የቅንጦት አፓርትመንቶችን እና የንግድ/ቢሮ ህንፃዎችን በመገባት ጥሩ ልምድ አካብቷል።
ድርጅታችን ከ50 በላይ ብቁ ባለሙያዎች ያሉት ሲሆን፣ ዋና አላማችንም ደንበኞቻችንን በበቂ ሁኔታ ማገልገል እና ከአፍሪካ ግንባር ቀደም የሪል ስቴት አገልግሎት ሰጪ መሆን ነው።
እስካሁን በዘርፋችን ታላቅ ጥራትን እና ጊዜውን ጠብቆ ማስረከብን በተመለከተ ጥሩ ስም የተቸርን ነን። ከኛ ጋር አብሮ መስራት ማለት በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ የሪል ስቴት ድርጅቶች ውስጥ በጣም ታማኝ የሆነውን ድርጅት አጋርዎ ማድረግ ማለት ነው።